ወደ የሰላም የምክር አገልግሎት እንኳን በደህና መጡ
እኔ፣ የተመዘገብኩኝ የ British Association of Counselling and Psychotherapy (BACP) አባል ነኝ። የኔ ዋንኛ ስነ ምግባራዊ በሆነ መንገድ እየሰራው ለእርስዎ ከእደጋ ነጻ የሆነና ሚስጥሩ የተጠበቀ ቦታ ለእርስዎ ማዘጋጀት ነው። እኔ በሚያገጥምዎ የህይወት ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ በሚያደርጉት ጉዞው ላይ እንደረዳዎና፣ ህይወትን በተሻለ መንገድ ለመምራት የሚያስችልዎትን ድጋፍና ቁሳቁሶችን እርስዎን ለማሳጠቅ ነው የኔ አላማ።
በአንድ ላይ መስራት
______
ለኔ፣ በጣም ስኬታማ የሆነ ምክር ሊፈጸም የሚችለው፣ ተገልጋይ ከአደጋ ነጻ፣ ድጋፍ የሚያገኝና የሚደመጥ መሆኑ ሲሰማው ነው። በአንድ ላይ ሆነን፣ እርስዎ ሃሳቦችዎንና ስሜቶችዎን የሚዳስሱበት፣ ከፍርድ-ነጻ የሆንነ አካባቢ መፍጠር እንችላለን። እኔ ከ 16 እና በላይ ለሆኑ ከሁሉም የባህል ዳርቻዎች ለመጡ ግለሰቦች የምክር አገልግሎት እሰጣለሁኝ፣ እንሲሁም ደግሞ የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመፍታት ላይ እርዳታን እሰጣለሁኝ።
ከዚህም በተጨማሪ፣ በጨዋታ መልክ የሚሰጥ ህክምናና፣ ፈታኝ ባሕሪያዊ ያላቸውን ጨምሮ፣ ከተሰበጣጠሩ ዳርቻዎች ከመጡ ወጣቶች ጋራ አብሮ የመስራት ልምድ አለኝ።
በነጻ የሚሰጥ የ 30-ደቂቃ የምክር አገልግሎት እሰጣለሁኝ። እነዚህም ክፍለ ግዜዎች ፊት-ለፊት፣ በኦንላይን ወይም በቴሌፎን በመገናኘት ሊደረጉ ይችላሉ።
______
ስሜ ሰላም ዜርኤ ይባላል። እኔ ግለሰቦች የተመጣጠነና የተሟላ ህይወት እንዲኖራቸው የሚያስችል ድጋፍ የመስጠት ቁርጠኝነት ያለኝ የተመዘገብኩኝ የተወሃሃደና ሰብአዊነታዊ አማካሪ ነኝ። የፈውስ አሰጣጤ መንገድ የሳይኮዳይናሚክ፣ ሰብአዊነት፣ እና የ CBT ፈውሶችን ያቀናበረ ነው። እኔ፣ የ British Association of Counselling and Psychotherapy (BACP) አባል ነኝ። ይህም ከፍተኛ የስነ ምግባራዊ መመሪያ ደንቦችን መከተሌን ያረጋግጣል።
እኔ እንግሊዝኛ፣ አማርኛ እና ትግርኛ አቀላጥፌ ስለምናገር፣ ከተሰበጣጠሩ ዳርቻዎች የመጡ ደምበኞችን ለመደገፍ ያስችለኛል። የኔ መሰረታዊ እምነት፣ ለራስዎ የህይወት ታሪክ ዋና ባለሞያ እርስዎ ኖት። ስለ ሆነም፣ እኔ እዚህ ያለሁት፣ እርስዎ በሚያደርጉት የለውጥ ጉዞ ላይ እርስዎን አቅም ለማስታጠቅ ነው። የበለጠ ደስተኛ ህይወትን መፈለጉ ድፍረትን ይጠይቃል። እናም፣ እኔ እዚህ ያለሁት በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ እርስዎን ለመደገፍ ነው።
____
____